Eligible Disciplines in Amharic | ብቁ የሆኑ የሙያ ዘርፎች

Click for English Haga clic para español 点击查看中文 Dịch sang tiếng Vit Cliquez pour le français 한국어를 보려면 클릭하세요 


የሞንትጎመሪ
ካውንቲ የስነ ጥበብ እና ሂውማኒቲስ ካውንስል (AHCMC) የገንዘብ ድጋፍ ከዚህ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት በአንዱ ወይም ከአንድ በላይ በሚሆኑትን የሙያ ዘርፎች ዙሪያ የሚሰሩ የስነጥበብ እና/ወይም የሂውማኒቲስ ድርጅቶችን እና ግለሰብ አርቲስቶችን እና ምሁራንን ያካትታል 

ውዝዋዜ(ዳንስ)በታሪክ ውስጥ እውቅና ያለውን ወይም ዘመናዊ ስታይልን የሚከተል ኮሪዮግራፊን ወይም እንቅስቃሴን ያካትታል 

ፎልክ (Folk) እናባሕላዊስነጥበብ( Traditional Arts) የጋራ የብሔር ቅርስ የጋራ ቋንቋ ሃይማኖት ወይም የስራ ሙያ ላይ የተመሠረቱ ጥበብ ነክ መገለጫዎችን ያጠቃልላል እነዚህ ብዙ ጊዜ በቤተሰብ እና በማህበረሰቦች ውስጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ በምልከታ በአፈ ቃል እና በተግባር ከአንጋፋ እስከ ጀማሪ ባልሙያ ድረስ የሚተላለፉ ጥበባዊ ባሕሎች ናቸው 

ታሪካዊአስፈላጊእና/ወይምጽንሰሐሳባዊየሆኑየስነጥበብስራዎችእነዚህን የፈጠራ ሂደቶችን እና/ወይም የተወሰኑ ስራዎችን የሚያንፀባርቅ እና የሚተነተን ስራን ያጠቃልላል ለምሳሌ ትይንቶችን ኤግዚቢሽኖችን ወይም የስነ ጥበባዊ ቁሶችን ያካትታል 

ታሪክወይምማህበራዊሳይንሶችበሰው ልጅ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ ወይም ባህላዊ ልማት ስነዜጋ እና የታሪክ ወይም የማህበራዊ ሳይንስ መረጃዎችን ወይም እንቅስቃሴዎችን ከማህበረሰቡ ጋር የሚያጋራ ምርምርን ጥናትን እና ጽሁፍን ያጠቃልላል 

ቋንቋዎች፣የቋንቋጥናት(Linguistics)እና/ወይምስነጽሑፋዊጥበቦች(Literary Arts)እንዴት እንደምንግባባ እና ሀሳቦቻችን እና አስተሳሰቦቻችን እንዴት እንደሚከናወኑ እና እንደሚተረጎሙ ማጥናትን እና መተንተንን እና የአንድ የተወሰነ የስነጽሁፍ ክፍልን ወይም የስነ ጽሁፍ ስራን ማጥናትን ወይም መተንተንን ያካትታል 

የሚዲያስነጥበባት/Media Arts በሥነ ጥበባዊ አውድ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ እና ለመገናኛ ብዙኃን ኮምኒኬሽን የሚስማሙ ኤሌክትሮኒካዊ እና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረቱ ሥራዎችን ያጠቃልላል በየትኛውም ዘውግ (genre) ውስጥ የሚሰራ ፊልም ቪዲዮ ድምጽ ወይም በኮምፒዩተር ላይ የተመሰረተ የኪነጥበብ ፕሮዳክሽንን እና/ወይም ስርጭትን ያካትታል በተጨማሪም የረዥም ጊዜ የፕሮጀክት ክፍልም የገንዘብ ድጋፉን መመሪያዎች የሚያሟላ ከሆነ ግምት ውስጥ ይገባል 

ሙዚቃ በማንኛውም ዘውግ (genre) ውስጥ የተሰራ ኦርጅናል ሙዚቃ ማቅረብን መፍጠርን መቅዳትን እና ማሰራጨትን ወይም በታሪክ እውቅና ያላቸውን የሙዚቃ ቅንብሮችን እና/ወይም ስታይሎችን ያካትታል 

ፍልስፍና ስነምግባር እና/ወይም የሀይማኖት ንጽጽር (Philosophy, Ethics, and/or Comparative Religion) ጥናት ስለ ህይወት አላማ የሞራል እና የስነምግባር መለኪያዎች በህብረተሰቡ ውስጥ እንዴት እንደሚነሱ እና በሃሳቦቻችን እና በድርጊቶቻችን ምክንያቶች ዙሪያ የሚደረጉ የጽንሰሐሳብ ምርምሮችን እና/ወይም ጥናቶችን ያካትታል 

ታሪክን መተረክ (Storytelling) በንግግር የሚቀርቡ ትይንቶችን ያጠቃልላል በተለይም የአሳታፊ ስልትን ተግባራዊ በማድረግ ቃላቶችን እና ድርጊቶችን በመጠቀም እና ሌሎች የታሪኩን አካላት እና የታሪኩን ምናባዊ ምስሎች በማሳየት የአድማጩን ምናባዊ አቅም የሚያበረታታ ነው 

ቲያትር(Theater) ኦሪጅናል ወቅታዊ ወይም ታሪካዊ እውቅና ያላቸው የቲያትር እና የሙዚቃ ቲያትር ስራዎችን መፍጠርን ማዘጋጀትን እና/ወይም ማቅረብን ያካትታል 

ስነጽሁፍ ነባራዊ የሆኑ የጥበብ ስራዎችን መፍጠር ማቅረብ እና ማሰራጨትን ያጠቃልላል ብሎም ህትመቶችን ንባቦችን እና ግጥሞችን፣ልቦለዶችን ልቦለድ ያልሆኑን ስራዎችን ልቦለድ ያልሆኑ እውነተኛ ታሪኮች የስክሪን ድራማዎችን እና የጨዋታ ስክሪፕቶችን ያካትታል 

ቪዥዋል አርት (Visual Art) የቪዥዋል አርቶችን መፍጠር ማዘጋጀት እና/ወይም ኤግዚቢሽን ማሳየት ላይ ያተኩራል በስፍራው ላይ የሚከናወኑ ወይም ጋለሪውን ማእከል ያደረጉ የጥበብ ስራዎች በማናቸውም የቪዥዋል አርቱ (Visual Arts) አካባቢ የሚገኙ ቁሶችን እና የሚገጣጠሙ እቃዎችን ያካትታል እነዚህም እንደ ባሕላዊ እና ዘመናዊ የጥበብ ስራዎችን የሚያስፋፉ የስነ ጥበብ (curatorial) ፕሮጀክቶች እና /ወይም ፕሮጀክቶች ተደርገው ይቆጠራሉ 

ዲዛይን ብዙ የሙያ ዘርፎችን ያቀፈ ሲሆን አርክቴክቸር ኮሙኒኬሽን እና ግራፊክ ዲዛይን ፋሽን ዲዛይን ታሪካዊ ቅርስ ጥበቃ የኢንዱስትሪ እና የምርት ዲዛይን የቤት ውስጥ ዲዛይን የአካባቢ ጥበቃ አርክቴክቸር(landscape architecture) የማህበራዊ ተፅእኖ ዲዛይን(social impact design) የገጠር አካባቢ ዲዛይን እና የከተማ ዲዛይን (የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስራዎችን የግንባታ ወጪዎችን እና የቦታዎችን ግዢ ወይም ኪራይን ሳይጨምር) ጨምሮ ብዙ ዘርፎችን ያጠቃልላል 

የተለያዩ የሙያ ዘርፎችን ያካተቱ አንድ ያደረጉ እና/ወይም ያቀናጁለእይታ የሚቀርቡ እና/ወይም ሁለገብ ስራዎች  ስራዎቹ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች መካከል ያሉ ልዩነቶችን መመርመር ማካተት ወይም የሙያ ዘርፎችን ማሻሻል እና በአዲስ መልክ ሊገለጹ የሚችሉበትን መንገድ መፈለግ ላይ ሊያተኩሩ ይችላሉ ፕሮጀክቶች የተለያዩ ወይም የበርካታ ባለሙያዎች ጥምር ሊሆኑ ይችላሉ እና የጥበብ ትይንቶችን የቪዥዋል የሚዲያ ዲዛይን የስነጽሑፋዊ ጥበቦችን እና/ወይም የሂውማኒቲስ የሙያ ዘርፍ ስራዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ