Cultural Plan Glossary in Amharic | የቃላት መፍቻ

Click for English Haga clic para español 点击查看中文 Dịch sang tiếng Vit Cliquez pour le français 한국어를 보려면 클릭하세요 


የሞንትጎሜሪ ካውንቲ ነዋሪዎች ኪነ
ጥበብ እና ባህልን በሰፊው እንደ “የታሪክ ቅርስን የሚያከብር እና የሚያቆይ የግል ወይም ባህላዊ ጠቀሜታ ያለው የሆነ ነገርን መፍጠር ወይም መስራት፣ ሀሳቦችን/እሴቶችን ማንፀባረቅ ወይም መፈተን፣ አዲስ ነገሮችን መፈተሽ፣ እና በውስጥ የሚከሰት ወይም በሚታወቁ ቦታዎች ውስጥ የሚንጸባረቅ እና የባለቤትነት ስሜትን የሚያጠናክሩ ወይም የእሱን አለመኖር ይገልጻሉ። 

በዚህ ግንዛቤ ላይ ተመስርተን፣ በባህ ዕቅድ ሂደት ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ ቁልፍ ቃላትን የያዘ የቃላት መፍቻ ፈጠረናል 


ኪነጥበ/ “ኪነጥበቦች”

ኪነጥበቦች ችሎታን፣ ፈጠራ እና የሚያምሩ ዕቃዎችን፣ አካባቢዎችን፣ ምርቶችን ወይም ተሞክሮዎችን ለመፍጠር የሚያስችሉ ሐሳቦችን የሚያካትት  የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ስብስቦችን (ለምሳሌ ስዕል፣ ስነጥበባት፣ ሙዚቃ፣ ቲያትር፣ የዳንስ ስነጽሑፍ እና ሌሎችም) ያካትታሉ። ምሳሌዎቹ የሚያካትቱት፦ 

  • የዕይታ ሰነ ጥበባት፦ ስዕል፣ ስነጥበባት፣ አርክቴክቸር፣ ሸክላ ሥራ፣ ስእል መሳል፣ ፊልም ማዘጋጀት እና ፎቶግራፍ ማንሳት  
  • የኪነ ጥበባት ዝግጅቶችን፦ ዳንስ፣ ሙዚቃ እና ቲያትር  
  • የስነ ጽሑፍ ስነ ጥበባት፦ ልብ ወለድ። ድራማ፣ ግጥም፣ እና ስድ ንባብ   
  • የሚዲያ ስነ ጥበባት፦ ፊልም፣ ቪዲዮ፣ እና የአሃዝ ስነ ጥበባት  
  • የሁለገብ ስነ ጥበባት፦ የተለያዩ ኪነ ጥበቦችን ማዋሃድ (ለምሳሌ ኦፔራ፣ ሙዚቃን፣ ድራማን እና የሥዕል ቅብን የሚያጣምር)  
          ባለቤትነት

          የሰዎች የባለቤትነት ስሜት የሚልቅ ትርጉም ያለው ህይወት ጋር፣ ከሚኖሩበት ስፍራ እና ከሚኖሩበት ቦታ ነዋሪዎች ጋር የመተሳሰር እና አብረው ከሚኖራቸው ሰዎች ጋር ተሳስሮ መኖር እና  ከራሳቸው በላይ የሆነ ነገር አካል መሆን ጋር የተያያዘ ነው። ይህም ከሚመለከታቸው መብቶች እና ኃላፊነቶች ጋር መኖር መቻል ማለት ነው። 

          የባህል ዘርፍ

          የባህል ዘርፍ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ዓይነቶችን፣ የፈጠራ ስራዎችን እና ባህላዊ ልምዶችን እንዲሁም እነሱን የሚደግፉ ድርጅቶችን እና ስፍራዎችን ያካትታል።  እነዚህ እንቅስቃሴዎች ለማህበረሰባችን ባህላዊ እና አንዳንድ ጊዜ ኢኮኖሚያዊ እሴትን ይጨምራሉ።  የባህል ዘርፉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን፣ ንግድ ድርጅቶችን እና የመንግስት ድርጅቶችን ያካትታል። 

          የባህል እንቅስቃሴዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶችን፣ ሙዚቃ፣ ስነ ጽሁፍ፣ ፊልም ንድፍ፣ የዕድ ጥበብ፣ ሰብዓዊነት እና ምግብ ማብሰል ናቸው። በተጨማሪም ሙዚየሞች፣ የሥዕል ጋለሪዎች፣ ቤተ መጻሕፍት እና ማህደሮች፣ የባህል ድረ ገጾች እና ቦታዎች፣ የባህል ድርጅቶች፣ በዓላት እና የሃይማኖት አከባበሮች፣ የማህበራዊ እና ባህላዊ ዝግጅቶችን ጭምር ያካታሉ።  

          ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶች የሚያካትቱት የኪነ ጥበብ ትምህርት፣ የኪነ ጥበብ ዕቃዎች፣ መደብሮች፣ የኪነ ጥበብ አገልግሎቶች፣ ማስታወቂያ እና የገበያ ስልቶች፣ ግራፊክ ዲዛይን፣ ፊልም እና ቴሌቪዥን ምርት፣ ለፈጠራ ሰዎች እና የባህል ቡድኖች የሚያግዙ የፋይናንስ፣ የሕግ እና የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ናቸው። 

          ባህል/ቅርስ

          ባህል ወይም ቅርስ የሚገልጸው የተወሰኑ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም የብሄራዊ ሥርዓቶች ጋር የሚዛመዱ  ምግብ አዘገጃጀት እና የባህላዊ ምግቦች፣ የተለያዩ ዕቃዎች መፍጠር፣ በዓላት እና ተጨማሪ ነገሮችን ነው።

          የፈጠራ ኢኮኖሚ (ምጣኔ ሀብት)

          ጠራሪ ኢኮኖሚ የሚያመለክተው ፈጠራን እና የባህል ሀብቶችን በመጠቀም አዳዲስ ሀሳቦችን ለማምረት፣ ስራ ለመፍጠር እና የአንድ ክልል ኢኮኖሚያዊ እድገትን እና ባህላዊ ሕያውነትን ለማሳደግ የሚያገለግሉ የኢኮኖሚ (የምጣኔ ሀብት) እንቅስቃሴዎችን ነው። እንደ ኪነ ጥበብ፣ ዲዛይን (ንድፍ)፣ ቴክኖሎጂ ዘርፎችን ያካትታል እና መጠነ ሰፊ የፈጠራ ስራዎችን ለማካተት ከባህላዊው ኢንድስትሪዎች በላይ ይሸፍናል።

          የባህል ዕቅድ

          የባህል ዕቅድ ማውጣት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮችን የሚለይ፣ መዋዕለ ንዋዮችን የሚመራ፣ ስለ ስነጥበብ እና ባህል በተመለከተ ለአካባቢው ፖሊሲዎች ማሳወቅ ስራ የሚሰሩ በቦታ ላይ የተመሰረቱ ዕቅዶችን የመፍጠር ተግባር ነው። በተለምዶ፣ የባህል ዕቅዶች አንድ አካባቢ እንዴት የሚከተሉትን እንደሚፈጽም ያግዛል፦  

          • የመንግስት እና የግል ዘርፍ ገንዘቦችን መጠቀም  
          • ተቋማትን መገንባት  
          • ደንቦችን ማውጣት ወይም መቀየር  
          • የህዝብ ቦታዎችን እና የመንግስት ህንፃዎችን መጠቀም  
          • የኢኮኖሚ ልማት እና ቱሪዝምን ማበረታታት  
          • የትምህርት ወይም የስነ ጥበብ ፕሮግራሞችን መደገፍ  
          • በካውንቲው ውስጥ ስነ ጥበባትን እና ባህልን የሚነኩ ሌሎች ውሳኔዎችን መወሰን  
                      የባህል ዘርፍ መካችነት

                      የባህል ዘርፍ መካችነት ማለት አርቲስቶች፣ የባህል ተቋማት እና የፈጠራ ኢኮኖሚ ንግድ ድርጅቶች የአመራር ወይም የሰራተኞችን ለውጦች፣ የሚቀያየር የታዳሚ ምርጫዎች ለውጥን፣ የማህበረሰብ መቀየርን፣ ወይም የገንዘብ ሁኔታዎችም እና በተፈጥሮ አደጋዎች እና በመንግስት ፖሊሲ ለውጦች ምክንያት የሚፈጠሩ መቋረጦችን ለመቋቋም የሚያስችል ችሎታ ነው።

                      ሰብዓዊነቶች

                      ሰብዓዊነቶች የሚያክትቱት የሰው ልጅ ባህሎችን፣ ሐሳቦች፣ ለማዶችን፣ እና ተሞክሮዎች ላይ ዘርፈ ብዙ ሁኔታዎችን ለመረዳት እና ለመጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት ናቸው። እነዚህ ምድቦች የሚያሳዩት የተለያዩ ማህበረሰቦች በጊዜ ሂደት እንዴት እንደተሻሻሉ እና እንዴት እንደተቀየሩ ነው። ሰብዓዊነቶች በተለምዶ የሚያካትቱት እንደ አንትሮፖሎጂ፣ አርኪዮሎጂ፣ ሶሾሎጂ፣ ታሪክ እና የባህል ጥናቶች የመሣሰሉ ትምህርቶችን፣ ሥነ ምግባር፣ ፍልስፍና፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ ጥናቶች፣ የኪነ ጥበብ ታሪክ፣ ስነ ጽሁፍ፣  እና የሚዲያ ጥናቶች ናቸው። ሰብዓዊነቶች አብዛኛን ጊዜ የተመራማሪ ሥራዎችን ያካትታሉ ነገር ግን በማህበረሰብ ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎችን ያካትታሉ። 

                      ተቆራኝነት

                      በአጠቃላይ ተቆራኝነት ማለት የሁለት ነገሮች የመደራረብ ሀሳብ፣ እርስ በእርስ መተላለፍ፣ እና የሆኑ ነጥቦች ላይ መገናኘት ማለት ነው። ለዚህ ዓላማ ሲባል፣ ተቆራኝነት ማለት የማህበረሰብ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚረዱ ስነ ጥበባትን፣ ባህልን እና ሰብአዊነትን መጠቀም ነው። በተለይም የባህል ዘርፍ/የፈጠራ ኢኮኖሚ ከመንግስት እና በአካባቢው ውስጥ የሚገኙ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች (NGOዎች) ጋር የሚገናኙበት መንገዶች እንደ መኖሪያ ቤት፣ ኢኮኖሚ ልማት፣ ደህንነት/ጤና፣ ትምህርት፣ የማህበረሰብ ግንባታ እና የአካባቢ ጥበቃ ባሉ ጎራዎች ላይ እሴት ለመጨመር የሚረዱ አዳዲስ መንገዶች ናችው።

                      እነዚህን የቃላት መፍቻዎችን ስናዘጋ የሚከተሉትን መጣጥፎች ዋቢ አድርገናል፦ 

                      1. Borrup, Tom. 2018. “Cultural Planning at 40 – A Look at the Practice and Its Progress.” Creative Community Builders 
                      2. MJR Partners. 2022. “Reflective Conversations on Arts and Culture: Observations and Understanding.” Arts and Humanities Council of Montgomery County. 
                      3. “National Endowment for the Humanities.” 2025. The National Endowment for the Humanities. January 14, 2025. https://www.neh.gov/home-2024. 
                      4. Whang, Vanessa, Communities in Collaboration | Comunidades en Colaboración, Alex Werth. 2018. “Belonging in Oakland: A Cultural Development Plan.” Cultural Affairs Division, City of Oakland, CA.